Are you a health professional? A doctor, a nurse or a physiotherapist? Are you a nutritionist, chef or social worker? You can register HERE to avail yourself for payable service

Blog

Blog

Essential Fatty Acids – ጠቃሚ የቅባት ምግቦች

Essential Fatty Acids – ጠቃሚ የቅባት ምግቦች

የቅባት ምግቦች በብዙ ሰዎች የሚዘወተሩ የምግብ አይነቶች ናቸው፤ ነገር ግን በይዘታቸው የግድ የማያስፈልግ ቅባት (saturated fats) ወይም ጠቃሚ ቅባት (polyunsaturated fats) ሊሆኑ ይችላሉ። የግድ የማያስፈልጉ ቅባቶች (Non-essential Fats) ° በሰውነታችን ሊመረቱ የሚችሉ በመሆኑ ለሰውነታችን የግድ አያስፈልጉም። ° በተለይ በአብዛኞቹ የእንስሳት ውጤቶች (ከአሳ በስተቀር)፣ በከፍተኛ ሁኔታ የተቀነባበሩ ምግቦች እንዲሁም  በይዘታቸው የረጉ ዘይቶች ውስጥ በስፋት ይገኛል። ° ስለዚህ እነዚህን የመሳሰሉ ምግቦችን መቀነስ ያስፈልጋል። በይዘታቸው የረጉ ዘይቶችን፣ የዶሮ ቆዳ እና ስብ ስጋን ደግሞ ፍፁም ማስወገድ ሊያስፈልግ ይችላል። °°°ጠቃሚ ቅባቶች (Essential Fats) ° በሰውነት ውስጥ የማይፈበረኩ፣ ሰውነታችን ከምግብ ብቻ ሊያገኛቸው የሚችሉ የቅባት (fat) አይነቶች ናቸው። ጠቃሚ ቅባቶች የሚባሉት:- – ኦሜጋ 3፣ (ሊኖሊክ አሲድ) – ኦሜጋ 6፣ (አልፋ ሊኖሊክ አሲድ) 1- ኦሜጋ 3  ቅባት ° የልብ እና ደም ስር ጤንነትን ይጠብቃል። ° ጠቃሚ ኮሌስትሮልን (HDL) በሚፈለገው መጠን ከፍ ያደርጋል። ° መጥፎ ኮሌስትሮልን (LDL) መደሚፈለገው መጠገን ዝቅ ያደርጋል (ያሻሽላል) ° የጠጣር የደም ስር ስብ (Atherosclerosis) መፈጠርን ይከላከላል።   በዚህም ሁሉ የልብ ህመም፣ ስትሮክ፣ የእግር ደም ስር መዘጋት ወይም ጋንግሪንን ከመሰሉ  የጤና ችግሮች ይከላከላል። በኦሜጋ-3 ቅባት የበለፀጉ ምግቦች – የተለያዩ የአሳ ዝርያዎች (ለምሳሌ ሳልመን፣ ቱና ፣ ሰርዲን) – የአሳ ዘይት – አኩሪ አተር፣ እና የአኩሪ አተር ዘይት – ተልባ እና የተልባ ዘይት – Walnut ለውዝ – ሱፍ እና የሱፍ ዘይት – ሰናፍጭ – ቦሎቄ 2- ኦሜጋ 6 ቅባት – የበሽታ መከላከልን ያሻሽላል በኦሜጋ-6 ቅባት የበለፀጉ ምግቦች – የኑግ ዘይት – የበቆሎ ዘይት – የሱፍ ዘይት – ለውዝ ° አመጋገብ °° ጠቃሚ የቅባት ይዘት ያላቸውን በየቀኑ ቆሎ፣ ፍትፍት፣ ዘይት፣ ጭማቂ እና በተለያዩ መንገዶች በመጠኑ መመገብ ቢቻል በተለይም የልብ እና የደም ስር ጤንነትን ለመጠበቅ ያግዛል። ° በተለይም ከስኳር ጋር የሚኖሩ ከሆነ፤ ለጤንነትዎ በየዕለት የምግብ ሜኖ ላይ ጠቃሚ  ቅባቶችን በመጠኑ ይጨምሩ።

@rihrahe_DM

Write a Comment

Select the fields to be shown. Others will be hidden. Drag and drop to rearrange the order.
  • Image
  • SKU
  • Rating
  • Price
  • Stock
  • Availability
  • Add to cart
  • Description
  • Content
  • Weight
  • Dimensions
  • Additional information
Click outside to hide the comparison bar
Compare