ፆም፣ የስኳርን መቀነስ መከላከል እና በጊዜ ራስን መርዳት
ፆም፣ የስኳርን መቀነስ መከላከል እና በጊዜ ራስን መርዳት (Fasting , Preventing and Self managing Hypoglycemia)
የስኳር መቀነስ (hypoglycemia) በደም ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን ከሚፈለገው በታች ዝቅ ሲል የሚከሰት ሁኔታ ነው። ይህም በአብዛኛው ስኳር ከ 70 mg/dl በታች ሲሆን ነው። በፆም ወቅት በትኩረት ልንከታተለው የሚገባን አንዱ ትልቅ አደጋ የስኳር መቀነስ ነው።
እንዴት መከላከል ይቻላል?
1- በፆም ሰዓት ከፍተኛ አካላዊ እንቅስቃሴን መቀነስ
2- ከፃም በፊት ባለው ቀን ዘግይቶ ምግብ መውሰድ ( ለምሳሌ በክርስቲያን ምሽት ላይ ዘግይቶ እራት መመገብ፣ ለረመዳን የሱር ሰዓትን ማዘግየት)
3- ግሊበንክላማይድ (Glibenclamide) እየወሰዱ ከሆነ ከሃኪም ጋር በመመካከር መቀየር
4- ኢንሱሊን እየወሰዱ ከሆነ ከሃኪም ጋር በመመካከር የመጠን ለውጥ ማድረግ
ምልክቶቹ
– ላብ ላብ ማለት፣
– የድካም ስሜት
– የእጅ (ሰውነት) መንቀጥቀጥ
– የልብ ምት መሰማት
– ብዥታ
– ከፍተኛ የረሃብ ስሜት
– ግራ መጋባት
– ራስ ምታት
– ሲዘገይ ራስ እስከ መሳት ይደርሳል
ራስን መርዳት
– የስኳርን መጠን ወዲያው መለካት ከተቻለ፣ በፍጥነት መለካት ( ነገር ግን ይህ ግዴታ አይደለም)
– እየፆሙ ከሆነ ፆም መስበር፣ ወዲያው ማግኘት የቻሉትን ምግብ መመገብ
– ከረሚላ፣ ለስላሳ፣ ጁስ ስኳርን ወዲያው በተወሰኑ ደቂቃዎች ውስጥ ወደ ጤናማ መጠን ሊመልሱ ይችላሉ
– ከ 15 ደቂቃዎች በኋላ ድጋሚ ራስን መለካት
Telegram: @rihrahe_DMcare @rihrahe_diabetesCare
ሁለንተናዊ ጤና በቤትዎ!