Are you a health professional? A doctor, a nurse or a physiotherapist? Are you a nutritionist, chef or social worker? You can register HERE to avail yourself for payable service

Blog

Blog

ስኳር ሙሉ ለሙሉ ሊድን ይችላል?

ስኳር ሙሉ ለሙሉ ሊድን ይችላል?

ብዙ ከስኳር ጋር የሚኖሩ ሰዎች መድኃኒት በማይወስዱበት ሁኔታ የስኳር መጠናቸውን ጤናማ (normal) ወደ ሆነ መጠን መመለስ ተችሏል።

ስኳርን መመለስ(Reversing)፦ ማለት ቀድመው ከስኳር ጋር የሚኖሩ ሰዎች፦ መድኃኒት በማይወስዱበት ሁኔታ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ወደ ነበረበት ጤናማ መጠን መልሶ ማቆየት ማለት ነው።

አመጋገብ፣ አኗኗር እንዲሁም የሰውነት ክብደት ላይ በሚመጡ በባለሙያ የታገዙ ተከታታይ ለውጦች ነው አሁን ከብዙ ከስኳር ጋር ከሚኖሩ ሰዎች ስኳርን ወደ ቀደመው ጤናማ መጠን መመለስ (reverse, remission) የተቻለው ። ነገር ግን ይህ የሚፀናው የመጡት የአኗኗር ለውጦች ሲቀጥሉ ብቻ ነው።

ስኳርን መመለስ (reversing) ከተሳካም በኋላ፦ የአኗኗር ፣ አመጋገብ እና የሰውነት ክብደት ሁኔታ በመልካም ሁኔታ ካልቀጠሉ የስኳር መጠን ድጋሜ ሊጨምር ይችላል ። በዚህም ምክንያት እስካሁን ባለው ቴክኖሎጂ ስኳርን ሙሉ ለሙሉ መፈወስ አልተቻለም። ተገቢውን የአኗኗር ለውጥ በማምጣት ብዙዎች መመለስን ሊያሳኩ እና ሊያስቀጥሉት ይችላሉ። ይህ እንኳን ሙሉ ለሙሉ ባይሆን ጥሩ የስኳር ቁጥጥር ይመጣል። ሰኳርን ለማስተካከል ያስፈልግ የነበረው የመድኃኒት መጠን ሊቀንስ ይችላል፤ ከምንም በላይ በስኳር ምክንያት የሚመጡ መዘዞችን መከላከል እና ማዘግየት ይቻላል። የአኗኗር፣ የአመጋገብ አና የሰውነት ክብደት ለውጥ አላስፈላጊ የጤና ተፅዕኖ እንዳያመጣ እና ሚዛናዊነቱን እንዲጠብቅ በባለሙያ ቢደገፍ ይመረጣል።

Write a Comment

Select the fields to be shown. Others will be hidden. Drag and drop to rearrange the order.
  • Image
  • SKU
  • Rating
  • Price
  • Stock
  • Availability
  • Add to cart
  • Description
  • Content
  • Weight
  • Dimensions
  • Additional information
Click outside to hide the comparison bar
Compare